ዶ/ር አብይ አህመድና የማጭበርበር የዲፕሎማሲ መንገዱ

በ ገብረመስቀል ካሳ (ቀድሞ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የፕረዚዳንት ፅቤት ሀላፊ)

በጥቅምት ወር 2013 ዓ/ም ምናልባትም ከትግራይ የዘር ማፅዳት ዘመቻ አስር ቀን ቀደም ብሎ ኣብይ ኣሕመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ መንግስት የሚከተለው የዲፕሎማሲ መንገድ “የማጭበርበር መንገድ ነው፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ህጎችና ስምምነቶችም ገሚሰቹ በግላጭ እያወቀን እንጥሳቸዋለን፣ ገሚሶቹ ደሞ እያወቅን ግን ደሞ ለዓለም ማሕበረሰብ እንዳላወቅን በማስመሰል እየጣስን የሀገራችን ልማት እናፋጥናለን፣ ስለዚህ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ አመራር ይህን መገንዘብና መተግበር ግድ ይለዋል” ብሎን ነበር። ስለዚህ ዶ/ር ኣብይ ኣሕመድ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት መመራት ያለበት በማጭበርበር ነው ብሎ የሚያምን መሪ ነው። በሰኔ ወር ከመቐለ በቅርብ ርቀት የምትገኝ ቶጎጋ የተባለችው የገጠር ቀበሌ ከተማ በኢትዮጵያ አየር ሃይል በትግራይ የሰማዕታት ቀን ሆን ተብሎ ከደበደበ በሗላ፣ የሰራውን ወንጀል ለመከላከልና አጀንዳ ለማስቀየር የክልሉ ጊዝያዊ አስተዳደር ካቢኔ አባላት “የትግራይ ሀይሎች ሲቪልያንን ገደሉ” ብለን መግለጫ እንድንስጥ ከፌደራል መንጎስት ትዕዛዝ ወርዶ ነበር። ይህንን መግለጫ እንደማናወጣና ይልቁንስ “የኢትዮጵያ አየር ሀይል ሲቨላያንን ጨፈጨፈ” ብለን ነው የምናወጣው ብለን ስለሞጎትንና በጉዳዩ ከፍተኛ ጭቅጭቅ ስለተፈጠረ የፌደራል መንግስት ከኣዲስ ኣበባ በራሱ በትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ስም “የትግራይ መከላኪያ ሀይሎች የጊዝያዊ አስተዳደር አመራሮች ገደሉ” ብሎ መግለጫ አወጣ።

በሰኔ ወር የኢትዮጵያ መከላኪያ ሃይልና የኤርትራ ሰራዊት በቅንጅት ዶ/ር ደብረፅዮንንና ጌታቸው ረዳን በእጅ ይዘን እናስመጣለን ብሎ በቆላ ተምቤን ቁጥር ስፍር የሌለው የፈሰሰው ሰራዊት ከ 11 ሰኔ 2013 ዓ/ም እስከ 21 ሰኔ 2013 ዓ/ም በትግራይ መከላኪያ ሃይሎች ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ። በዚህ የተናደደው መከላኪያ ሀይልም መላ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር አመራሮችን በአክሱም ሆቴል ውስጥ እንድንቆይና እንዳንቀሳቀስ ትዕዛዝ ከተሰጠን በሗላ፣ መጨረሻ ስዓት ላይ የፌደራል መንግስቱ ታማኝ ያላቸውን አመራሮች በአውሮፕላን አስወጥቶ እኛን ለመግደል አሴረ። ሁኖም በጊዝየው እኔ ጉዳዩን ስለነቃሁበት በራሳችን መንገድ የዕዝ ሰንሰለቱ ጥሰን ወደ ዓፋር በመኪና ወጣን። የአብዓላ ቁልቁለት እየወረድን ሳለ እንደተለመደው የፌደራል መንግስት “የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት በትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት አውጃለሁ” ብሎ ሲናገር እኛም እንደ ማነኛው የኢትዮጵያ ዜጋ በመኪናችን ውስጥ፣ በአስቸጋሪው የመንገድ ጉዞ ሁነን ሰማን። ከትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር በጉንበት ወር የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ የጠየቅነው ጥያቄ በጊዜው በከፍተኛ ቁጣና ዘለፋ ውድቅ እንደተደረገ ግን መላው የትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ካቢኔ ያውቋል።

በወርሀ መጋቢት፣ ሚያዝያና ጉንበት ለአውሮፓ ህብረትና ኣሜሪካ እንዲሁም ሌሎች ዲፕሎማቶች በምዕራብ ትግራይ የዘር ማፅዳት ወንጀል እየተፈፀመ ስለሆነ እንዲያቁመትና፣ በተስፋፊው የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚልሻና ፋኖ እንዲሁም በኤርትራ ሰራዊት እርምጃ እንዲወሰድ፣ በትግራይ ለተፈጠረው ሰፊ ማህበራዊ ቀውስና ርሃብ መፍትሔ እንዲያበጁ ጠይቄያቸው ነበረ። ምላሻቸው በጎ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ይሄ ነው የሚባል እርምጃ ሳይወስዱ፣ 5.2 ሚልዮን ህዝባችን በከፋ ችጋር ውስጥ ገብቶ፣ ከአንድ ሚልዮን በላይ ህፃናትና ሴቶች በርሀብ አለንጋ እየተቀጡ፣ ከሁለት ሚልዮን ህዝባችን ከቀየውና ቤቱ ተፈናቅሎ በመንገድና በበረሃ ወድቆ፣ ለሰባት ወራት ያለ ደሞዝ፣ መብራት፣ ስልክ፣ የባንክ አገልግሎትና መድሓኒት አቅርቦት እየተሰቃየ ባለበት ሁኔታ እነዚህ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከተመሰረቱበት ዓላማና ራዕይ በተቀራኒ ቁሞ የበይ ተመልካች ሁኖ ሰንብቷል። ይህንን ጉዳይ የአፍሪካ ሕብረት፣ የአውሮፓ ሕብረትና ኣሜሪካ በአስቸኳይ ተጨባጭ እርምጃ ካልወሰዱ በትግራይ የዘር ማፅዳት ወንጀል ከሚጠየቁት አካላት በግምባር ቀደም የሚቀመጡት ይሆናል።

ከአንድ ወር በፊት የትግራይ መከላኪያ ሀይሎች አዲስ ኣበባ ደጃፍ ደብረብርሃን ላይ ሲደርሱ፣ ጅቡቲ የሚገኘው የኣሜሪካ ወታሃደራዊ ሀይል አዛዥ ጀነራል ዊልያም ዛና “ቀዳሚ ዓላማችን በምስራቅ ኣፍሪካ ለሚፈጠረው ቀውስ ወታሃደራዊ ምላሽ መስጠት ነው” ሲሉ ተደመጡ።ለገባው ሰው የትግራይ መከላኪያ ሀይል ቀፋፊውና ወንጀለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ለመጣል ከተንቀሳቀሰ ከላዩ ላይ እሳት አዘንባለሁ ዓይነት መግለጫ ነው። ትናንት በሶማልያው ፕረዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስተር ውስጥ በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት በደቂቃዎች ውስጥ “ወታሀደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተናል” ሲሉም ተደምጧል። ለማነኛውም ብቻውን የቆሞው የትግራይ ህዝብና መከላኪያ ሀይል ይሀ ነው የሚባል ዓለምአቀፍ ድጋፍ ሳያገኝ አንድ ዓመት ኣልፎታል። በማጭበርበር ዲፕሎማሲ የሚያመልከው ወንጀለኛው የኢትዮጵያ መንግስትና አጋሮቹም፣ በግልባጭ የትግራይ መከላኪያ ሀይል የኣሜሪካ መንግስት ተላላኪ በማስመሰል ሲሱሉት እያየን ነው። ጅቡቲ የተቀመጠው የኣሜሪካ ወታሀደራዊ ሀይልም በመጥፋት አፋፍ ላይ ያለውን የትግራይ ህዝብ የሰብአዊ እርዳታ ኮሪደሮች ማስከፈት አቅቶት ቁሞ ሲያይ እየተመለከትን ነው። የኤርትራ ወታደሮችም የትግራይ ዳር ደንበር ጥሶ በመግባት በሺዎች የሚቆጠሩት ሴቶች፣ መንኩሴዎች፣ አረጋውያንና ልጃገረዶች ሲደፍሩ ተጨባጭ መረጃዎች በእጁ ይዞ ቁሞ እየተመለከተ ነው።

እውነታን በገባን ልክ እንደምንተነትን የሚታወቅ ነው፡፡ እውነታው ግን የምንቀይረው አይሆንም፡፡አብይ አህመውድ በአለም አቀፍ ግንኙነት እርያ ሆነዋል፡፡ አለም የሚጠየፈው መሪ ሆናዋል ማለት ነው፡፡ የአብይ ነብስ ትላንት መስኩ አይበቃኝም ብላ እዩኝ እይኝ ስትል ከርማ ዛሬ ደብቁኝ ደብቁኝ እያለች ነው፡፡ አብይ ከእንግዲህ በመንደሩ የሚፎክር ኢሳያስ አፈወርቂ ሆነዋል ፡፡ በሌላ አነጋገር አብይ አህመድ በራሱ ፈቃድ የመንደር ሽማግሌ ለመሆን መርጠዋል፡፡ ትላንት የሸለመችው ዓለም ዛሬ እሱን ለማየት የምትጠየፍ መሆንዋን ቢገባኝም ተጨባጭ እርምጃ በአስተዳደሩ ለመውሰድ ስትቸገር ግን እያየን ነው፡፡ አብይ በስልጣን የሚቆይባቸው አመታት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ዕዳ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ኣብይ በስልጣን እስከቆየ ድረስ አገራችን የተነጠለችና ድሀ አገር ትሆናለች፡፡

የውጭው ግንኙነት የተወሰኑት የአለም ሀገራት የተስማማባቸው ወጎች ና እሴቶችን ማክበር ይጠበቅብሃል፡፡ አለም ጨዋ መሆንን ይጠይቃል፡፡ ጨዋነት አንዴ ከወረደ ተመልሶ አይመጣም፡፡ ችግሩ የአገር መሪ በአለም ሲዋረድ አገርም የሚያዋርድ መሆኑ ነው፡፡ ተወደደም ተጠላም አብይ በሰራው ወንጀል ከአለም ተገልለዋል፡፡ የጨዋነት አቅሙ ተሟጠዋል፡፡ አለም እሱን ትጠየፋለች፡፡ አፍሪካዊያንም ቢሆኑ አብይን ይጠየፍታል፡፡ ከውጭ ዓለም የተገለለ መሪ ለአገራችን የሚያስከትለው ጣጣ ለመተንበይ ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም፡፡ ጎረቤት አገራትን ማየት ነው፡፡ ቢያንስ ንአምን ዘለቀ የተባለው የባንዳ ርዥራዥ ልጅ የሚያቆለጳጵሳት ኤርትራን ማየት በቂ ነው፡፡

አብይ በትግራይ የዘር ማፅዳት ወረራ ከፈፀመ ወዲህ እየተነጠለ መጥተዋል፡፡ የፖለቲካ ልዩነት በጦሩነት ለመፍታት የሄደበት የተሳሳተ ኣካሄድ ቀድሞም ቢሆን የተወደደ አልነበረም፡፡ ኣብይ ጦርነቱ ሲጀምር በአጠረ ግዜ ጨርሶ እጁ ታጥቦ ከደሙ ንፁህ ነኝ ለማለት ነበር፡፡ ነገር ግን ራሱ በቀሰቀሰው ዘረኝት ወታደሮቹና ግብረ አበሮቹ በትግራይ መንደሮች ተሰምቶ የማይታወቅ የዘር ማፅዳት ግፍ ፈፀሙ፡፡ ይባስ ብሎ ቂመኛው ኢሳያስን ጋብዞ በትግራይ ህዝብ ላይ ተነግሮ የማያልቅ ወንጀል ተፈፀመ፡፡ ባሩድ የሸተተው ጎሮቤት የኣማራ ሽፍታም እንደነጋበት ጅብ ሃብትና መሬት ለመቀራመት ዘሎ ገባ፡፡ ሁሉም በወንጀል ውስጥ ገብቶ ተነከሩ፡፡

አብይ የረሳው ነገር የፖለቲካ ወንጀል ከፈፀመ መሪ መነካካት የሚፈልግ አገር የሌለ መሆኑ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ህግ መንግስታት ዜጎቻቸውን የመግደል መብት የላቸውም፡፡ ሉአላዊነት መብት የማክበር እንጂ የመግደል መብት አያጎናፅፍም፡፡ አብይ የሰራው ወንጀል በሁሉም ሰው መንገድ ላይ የቆመ ጋሬጣ ነው፡፡ እንቅፋት ነው፡፡ አሁን ሁሉም ወገን በስሜት ውስጥ በመሆኑ ይህን የሚያስብበት ወቅት አይደለም፡፡ ስለ ነገ የሚያስብበት ወቅት አይደለም፡፡ ነገን ግን መሸሸ አይቻልም፡፡

አብይ አህመድ በአጭር ግዜ ውስጥ የተሰጠውን ፀጋ፣ ኢትዮጵያን የምታክል ትልቅ ጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታ ያላት ሀገር ይዞ፣ ዓለም የተጠየፈውን ኢሳያስ ኣፍወርቂ እግር ሂዶ የወደቀ የባከነ አሳዛኝ መሪ ነው ፡ አለም ጨካኝ ናት፡፡ የትላንት ከንቱ ውዳሴና ሽልማት ለማስታወስ አትገደደም፡፡ ለዚሁ ቦታ የላትም፡፡ ችግሩ በሰራው ወንጀል የመከሰስ ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ እሱ የማይቀር የህግ ጉዳይ ነው፡፡ ወንጀል ስትሰራ ከአለም ትገለላለህ፡፡ ዲሞክራሲያዊ አለም ኣብይን ለመቀበል ፍቃደኛ አይሆኑም፡፡ ከእንግዲህ አውሮፓ መሄድ የለም፡፡ መሪዎች ካልቸገራቸው በስተቀር ወንጀል የሰራ መሪን ከመጨበጥ ይሸሻሉ፡፡ ወንጀል ማጠብ አይቻልም፡፡ አብይ የመንደር መሪ ሆኖ ሊቀጥል ይችላል፡፡ የውጭ የፍይናንስ እርዳታ፤ ኢንቨስትመንት ይቀራል፡፡ ፈጣን ልማት የሚባለው ወሬ ብቻ ይሆናል፡፡ አገሪቱ የስራ አጥ መናሓርያ ትሆናለች፡፡ የአገር ካፒታልም ይሸሻል፡፡ በአገር ውስጥም ቢሆን ውስጣዊ ዲሞክራሲያዊ ትብብር በአብይ ዘመን ሊከሰት አይችልም፡፡

እንዲህ ያሉ መሪዎች የህዝብን የችጋር ዘመን ያራዝማሉ፡፡ የኢሳያስ አፈወረቂን ማየት ይበቃል፡፡ ኢሳያስ ከመንደሩ ወጥቶ ቁም ነገር አይሰራም፡፡ ከአለም የተገለለ መሪ ነው፡፡ ሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀመ መሪ በአውሮጳና አሜሪካ ጎደናዎች ሊንሸራሸር አይችልም፡፡ ብራስልስ፤ ዋሽንግተንና ጄኔቭ መሄድ ኣይቻልም፡፡ ወደ ተጠቀሱት አገሮች የሚሄዱት እሱን የሸሹ ኤርትራዊያን ብቻ ይሆናሉ ፡፡

የከሸፈው የማጭበርበር ዲሎማሲ ስልት፣

ሰሙኑን ኢትዮጵያ ከአገዋ (AGOA) መሰረዝዋን ሰምተናል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሙሸንም (UNHRC) በአገራችን የተሰራው የሰብአዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ ቡድን እንዲጣራ ወስነዋል፡፡ ሁለቱም ብቻ ብንወስድ የአብይ መንግስት የዲፕሎማሲ ሚዛን ምን ያሕል እንዳዘቀዘቀ መገምገም እንችላለን፡፡ ቀደም ሲልም የአውሮጳ ሕብረት የሚሰጠው የፍይናንስ ድጋፍም ተሰርዘዋል፡፡ የኢትዮጵያ ግንኝነት የጦር መሳርያ ከሚሸጡ በሰብአዊና ዲሞክራሲ የሚታሙና የተገለሉ አገራት ብቻ እየሆነ ነው፡፡ ከቱሩክ፤ UAE፤ ከኢራን፤ ከሩስያ ሊገኝ የሚችል ጦር መሳርያ ብቻ ነው፡፡ ቱሩኮች አህመድ ግራኝን በጦር መሳርይ የረዱ ወገኖች ናቸው፡፡ ሩስያ ደርግን ስትረደ ነበር፡፡ እኒህ አገራት የሚታወቁት በአሉታዊ ጎኑ ነው፡፡ ስለዚህ አገራችን ከእነዚህ ጋር በመዛመድ ማደግ ትችላለች የሚል ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ በልመና ይቀናኛል ሲለን የነበረው አብይ ከአረብ በሻንጣ ሊረጠብ ይችል እነደሆነ እንጂ ለህዝብ የሚጠቅም ሊገኝ አይችልም፡፡ ከአገዋ መወገድ ያለው ትርጉም ማወቁ ተገቢ ነው፡፡ ከአገዋ መገለል የ100,000ሺ ሰራተኞች ስራ አደጋ ይወድቃል፡፡ በ100 ሚልዮን የሚገመት የውጭ ምንዛሪ ኣይገኝም፡፡ መንግስት ዲያስፖራ እንዲገቡለት የሚማጠነው ገንዘብ ፍለጋ ነው፡፡ የአሜሪካን ገበያ ትኩረት አድርገው ኢንቬስት ያደረጉ ቻይናዊያን ወደ ሌላ አገር ይሰደዳሉ፡፡ቻይናዊያን የውጭ ምንዛሪ ገቢ የሌላት አገር መቆየት አይፈልጉም፡፡ ቻይና ስለ እኛ ብላ የምትሰራው ተጨማሪ ነገር ይኖራል ብሎ መጠበቅ የዋሕነት ነው፡፡

በአንድ ጉዳይ መስማማት ያለብን ጉዳይ ቢኖር አብይ ከአራት ኪሎ ጎትቶ የሚያወጣው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ አለም አብይን የመጎተት ሃላፊነት የላትም፡፡ ግንኙነቱ ግን ተበላሽቷል፡፡ አገር ለማዳን ከሰውየው መገላገል ነው፡፡ ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ስቃይና መከራ እየተራዘመ ያለው። ኣሜሪካ የትግራይም ኣብይ የሚመራት የኢትዮጵያም ደጋፊ አይደለችም። ሁኖም የትግራይ መከላኪያ ሀይል ከደብረብርሃን በመመለሷ የትግራይም የኢትዮጵያም ህዝብ ስቃይና መከራ አራዝማለች።

የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሙሽን የአብይ ወንጀል በአለም አቀፍ ነፃ አጣሪ ቡድን እንዲጣራ መወሰኑ አብይ አሕመድ ምን ያህል እንደተገለለ ማሳያ ነው፡፡ መጀመርያ በአጀንዳ ያስያዙት ያደጉና የበለፀጉ የአውሮጰ አገራትና አሜሪካ ነበሩ፡፡ ከአብይ ጎን የቆሙት ሩስያና የተወሰኑ አፍሪካ አገራት ናቸው፡፡ውሳኔው በአብይ ሰፈር ድብ ዕዳ ነው፡፡ በመዶሻ መወቀጥ ነው፡፡ የአብይ መንግስት ገና አጀንዳው ተይዘዋል ሲባል በመግለጫ ጋጋታ ያደነቆረን ትልቅ ስጋት ስለፈጠረበት ነው፡፡ ውጤቱ በመተንበይ ብፍርሃት ተውጠዋል፡፡ የፈሰሰው የትግራይ ደም ድምፅ አውጥቶ እየጨሆ ነው፡፡ በአሁኑ ዘመን ነፃ እርምጃ አይቻልም፡፡ ሰው ገድለህ በሰላም መኖር እንዳማይቻል አሳይተዋል። የአብይ የማጭበርበር የዲፕሎማሲ መንገድም መክኗል።

ችግሩ አብይ በስልጣን እስከቀጠለ ድረስ የአገራችን መገለል የሚቀጥል መሆኑ ነው፡፡ ነገ ወንጀለኞች ለፍርድ አሳልፍቹህ ስጡ ወደ ሚለው ሲደረስ ዛሬ ሚድያን ያስቸገሩ ጄኔራሎች የሚደበቁበት ቀን ሩቅ አይደለም፡፡ በሰሩት ወንጀል ነገ ለአለም አቀፍ ፍርድቤት ተይዘው ይቀርባሉ፡፡ በመጨረሻም ለዚሁ ሁሉ ያደረሰን “ፍቅር ያሸንፍል” በሚል መፈክር ተሸፍኖ የመጣን ቡድን ለማስወገድ የዐለም ሀገራትና ተቋማት እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ቆመጥ ማንሳት ያስፈልጋል። ይህንን ባታደርጉ ግን እኔ የምነግራቹ በግልፅ ቋንቋ ነው፣ ትግራይ ብቻዋን ሀገር ብቻ ሳትሆን አህጉር ጭምር ናት፣ ኢትዮጵያ ያለ ትግራይ ግን ሀገር ሳትሆን መንደር ናት! ድል ለሰፊው ህዝብ!

ገብረመስቀል ካሳ፣ 20 ታህሳስ 2014 ዓ/ም

32 thoughts on “ዶ/ር አብይ አህመድና የማጭበርበር የዲፕሎማሲ መንገዱ

 1. Have you ever thought about adding a little bit more
  than just your articles? I mean, what you say is fundamental and everything.
  Nevertheless imagine if you added some great graphics or videos to give your posts more, “pop”!
  Your content is excellent but with images and video clips, this blog could undeniably be one of the very best in its field.
  Amazing blog!

 2. Sweet blog! I found it while browsing on Yahoo News. Do you have any tips
  on how to get listed in Yahoo News? I’ve been trying for a while but I never seem to get there!
  Many thanks

 3. Thank you for every other great post. Where else may anyone get that type of info in such an ideal way of writing?
  I have a presentation next week, and I am at
  the search for such info.

 4. Have you ever thought about including a little bit more than just
  your articles? I mean, what you say is important and all.
  However imagine if you added some great graphics or videos to give your posts more, “pop”!
  Your content is excellent but with pics and clips, this website could undeniably be one of the
  very best in its field. Great blog!

 5. Somebody essentially help to make critically articles
  I’d state. This is the very first time I frequented your website page and to
  this point? I surprised with the analysis you made to make this particular put up extraordinary.

  Fantastic activity!

 6. Hello There. I discovered your blog the use of msn. That is a
  very neatly written article. I’ll make sure to bookmark it and come back to learn more
  of your helpful info. Thanks for the post. I’ll definitely
  comeback.

 7. This design is wicked! You definitely know how to keep a reader
  amused. Between your wit and your videos, I was almost moved to start my own blog (well, almost…HaHa!)
  Great job. I really loved what you had to say, and more than that, how you presented it.

  Too cool!

 8. I feel this is among the most vital info for me. And i’m glad studying your article.
  But want to remark on some basic things, The website taste is great, the articles is in reality
  nice : D. Good process, cheers

 9. Hello, Neat post. There’s a problem together with your site in internet explorer, may check this?
  IE nonetheless is the marketplace leader and a
  large component to other folks will omit your excellent writing because
  of this problem.

Leave a Reply

Your email address will not be published.