የሃይማኖት አባቶች ስለ ሰላም አስፈላጊነት

የትግራይ ህዝብ እና መንግስት የሰላም አስፈላጊነት በመረዳት የወሰኑት ውሳኔ ሊመሰገን ይገባል – የሃይማኖት አባቶች

የትግራይ ህዝብ እና መንግስት ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ በመስጠት የትግራይ ሰራዊት ከአፋር እና አማራ ክልል አካባቢዎች እንዲወጣ የወሰኑትን ውሳኔ የሰላም በር ለመክፈት እድል የሚሰጥ እጅግ የሚደነቅ እና የትግራይ ህዝብና መንግስት ለሰላም ያላቸው ፍላጎት በግልፅ የሚያሳይ ውሳኔ ነው ሲሉ ከድምፂ ወያነ ቴሌቭዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት የሃይማኖት አባቶች ተናገሩ።

ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉት የሃይማኖት አባቶች የትግራይ ህዝብና መንግስትም ይህን የሰላም አስፈላጊነት በመረዳት የወሰኑት ውሳኔ በመሆኑ ሊመሰገን የሚገባው እና ሁሉም አካል ሊቀበለው የሚገባ ውሳኔ ነው ብለዋል።

ይሁን እንጂ የፋሽስት አብይ አህመድ ቡድን እና ተስፋፊዎቹ የአማራ ክልል ሃይሎች ግን በትግራይ ህዝብ እና መንግስት የቀረበውን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በማለት አሁንም በትግራይ ህዝብ ላይ የጄኖሳይድ ወንጀላቸው አጠናክረው መቀጠላቸውን የገለፁት የሃይማኖት አባቶቹ ፣ አለም አቀፍ ማህበረሰብም የትግራይ መንግስት ውሳኔ ከማድነቅ እና ከማመስገን ባለፈ በትግራይ ህዝብ ላይ ጄኖሳይድ እየፈፀሙ ባሉት ፋሽስታውያን እና ወራሪ ሃይሎች ላይ ተግባራዊ እርምጃ በመውሰድ የሰላም አማራጭ የሚፈጠርበት ሁኔታ መፍጠር ይገባቸዋል ብለዋል።

በተጨማሪም የትግራይ ህዝብ እንዲጨፈጨፍ ለፋሽስት ብዱኑ የጦር መሳርያ ድጋፍ እያደረጉ ያሉትን ሀገራትም አለም አቀፍ ማህበረሰቡ ጫና ሊፈጥርባቸው እና ማዕቀብ ሊጥልባቸው ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

Source: ድምፂ ወያነ ትግራይ (ታህሳስ 20/2014 ዓ/ም)