የውሸት ፊት አውራሪዎች

ከቅርብ ወራት ወዲህ የአብይ አህመድ የሳሎን ውሻ እየሆኑ ያሉት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ሀሰትን እንደ እውነት ለህዝብ ከመጋት ተሸጋግረው እርስ በርሱ የሚጣረስ የማይያዝ የማይጨበጥ መረጃ በማሰራጨት ህዝቡን ግራ እያጋቡት ይገኛሉ። ኢቢሲ የተባለው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ተነስቶ ለአማራ ህዝብ የተለያዩ መሰረታዊ ልማቶችን ሲሰጥ የነበረው የትግራይ ሰራዊት ከአማራ ክልል ንብረት ስለመዘረፉ ያወራል። ጀብደኛው የአማራ ክልል ሚዲያ ደግሞ ያልተፈጠረን፣ የሌለውን ድል ለመፈለግ ሲል የትግራይ ሰራዊት በደረሰበት ሞት አንድም ንብረት ሳይዝ የራሱም ንብረት ሳይቀር ጥሎ ተበታትኖ ወደ ትግራይ መመለሱን ያሰራጫል። አለፍ ሲልም ጣብያው መጀመርያ አባቴን ገደሉት ከዛም እኔን ገደሉኝ የሚሉ ጉደኛ ምስክሮች ይዞ ይቀርባል። አሁን ላይ መቶ የሚነሳ ሰው በህንድ ፊልሞች እንኳን እየቀረ ነው።

ህዝቡ አፈናውን በዝቶት ሪሞቱን አንስቶ ፋና የተባለው ሌላ የሳሎን ላይ ውሻ ጋር ሲቀይር የትግራይ ሰራዊት በአማራ ክልል የነበሩ ኢንዳስትሪዎች አውድሞ ስለመሸሹ ይበተረፋል። ይህ ዜና ሳይደርቅ ታድያ በአማራ ክልል 11 ኢንዱስትሪዎች በቀናት ውስጥ ስራ ሊጀምሩ ነው ብሎ ኢቢሲ የተባለው መገናኛ ብዙሃን ውሃ ይቸልስበታል። የማይሆኑ ሆኖው ከወደሙ እንዴት በቀናት ውስጥ ስራ ሊጀምሩ ቻሉ የሚል ጥያቄ የሚያነሳ ኢትዮጵያዊ እጅግ ትንሽ ነው።

ዋልታ የተባለው መገናኛ ብዙሃን ደግሞ ሀሰትን ከፍ አድርጐ ይመጣና በአማራ ክልል በግብርና ብቻ በ266 ቢልዮን ብር በላይ ውድመት ደረሰ ብሎ እንደጉድ ያዥጎደጉደዋል። እነዚህ ሰዎች ቢልየን እና ሚልየን መለየት አቅትዋቸው ነው ወይስ የሚል ጥያቄ የሚያነሳም ሰው ቁጥሩ አነስተኛ ነው። ደግሞም አንድ አንድ የሚጠሩት ቁጥር ከሀገሪቱ የዘርፉ በጀት በላይ ነው።

ይህ ሁሉ ተዘረፍን ወደመብን ለምን ይሆን የሚል ጥያቄ ሲነሳ ግን የዘፈን ዳርዳርታው እስክስታ እንዲሉ ከሰሙኑ ከወደ ባህርዳር እየተሰሙ ያሉ ድምፆች በቂ ምላሽ ናቸው። ልክ ከዚህ በፊት የትግራይን ሀብት ወደ ባህርዳር፣ ጎንደር እና አስመራ እንዳጓጓዙት ሁሉ አሁንም ይህንን ድብቅ ፍላጎታቸው በሚዲያቸው እያመለጣቸው ተቸግረዋል።

ጀግናው የትግራይ ሰራዊት በእምብርታቸውም አልፎ አዲስ አበባ አፍንጫ ድረስ ጠላቶችን እየደቆሰ ሲገሰግስ ልክ ውሃ ውስጥ እንደገባች አይጥ ፀጥ ረጭ ብለው የነበሩ የአማራ ክልል ኤሊቶች አሁን ላይ በፎከራ ለያዥ ለገናዥ እያስቸገሩ ናቸው። ህዝብን እንደህዝብ ለማጥፋት ያላቸው ውጥንም የትግራይ ሰራዊት ለሰላም እድል ለመስጠት ለቆ ከወጣ ብኋላ በጡሩንባቸው እያስለፈፉ ናቸው።

ጅግናው የትግራይ ሰራዊት የአማራ ክልል ተቋማትን ሲጠብቅ እናቶች ሲያዋልዱ ውሃ ሲያድል እና ወፍጮ ቤትን ሲያስጀምር የነበረ ቢሆንም ከህዝቡ ጋር መናበብ የተሳናቸው የአማራ ክልል አመራሮች የትግራይን ሰራዊትን ስም ጥላሸት መቀባታቸው ቀጥለውበታል። የወሎ ህዝብ የትግራይ ሰራዊት ነው ወይስ ፋኖ ነው የዘረፈው ጠንቅቆ ያቀዋል። እንኳን ሰው ከተሞቹ ሳይቀር በቂ ምስክር ናቸው።

Source: አንገሶም አብርሃ፣ ድምፂ ወያነ ትግራይ (ታህሳስ 21/2014ዓም)